Debre Genet Saint Michael Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Melbourne -በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደብረገነት  ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገፅ
  • ስለ ቤተክርስቲያናችን
  • የፎቶ ማህደር
  • ኩነቶች
  • ስብከቶች
    • ጠቃሚ ጽሑፎች
  • ዜናዎች
  • ያግኙን
  • ጉዞአችን
  • ይለግሱ
  • Search

Home

You are here: Home

የሰንበት ት/ት ቤት ለወጣቶችና ህፃናት አገልግሎታችን ትምህርተ ሐይማኖት የቅዱሳን ዓምድጠቃሚ ገፆች የዘመን መቁጠሪያ ኪነ ጥበብ

“ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን” 2ኛ ቆሮ 9፡15

የሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በብፁዕ አባታችን አቡነ ጴጥሮስ ልዩ ጥረት እና በብፅዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ መልካም ፍቃድ ሐምሌ 12 ቀን 2000 ዓ.ም ተቋቋመ፡፡

ከዚያም ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ቅዱስ አምላካችን የፈቀደው ሰዓት ሲደርስ መሬት ተገዝቶ እና የጊዚያዊ ቤተክርስቲያኑ ስራ ተጠናቆ ህዳር 12 ቀን 2007 ዓ.ም ቦታው ተባረኮ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ ይህንንም ቤተክርስቲያን ለመባረክ በፓትርያርካችን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና በቅዱስ ሲኖዶስ መልካም ፈቃድ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፡የሲዳማ እና አማሮ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ፡ የቤይሩት የተባበሩት አረብ ኢመሬትስ እና አካባቢው ሊቀ ጳጳስ ብዙ መንገዶችን ተጉዘው መሃላችን ተገኝተዋል፡፡

 

በአሁኑ ወቅት ደግሞ የምመናኑ ቁጥር በመጨመሩ ከቤተክርስቲያናችን አጠገብ ያለው መሬት ተገዝቶ ክፍያው በጥሩ ሁኔታ እየገፋ ይገኛል፡፡ ምዕመኑም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ይህንን አላማ ለማሳካት ገንዘብ እያዋጣ እንዲሁም በሚፈለገው ሁሉ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡ የዋናው ቤተክርስቲያን ስራም በቅርቡ ይጀመራል፡፡ ለዚህም የሁሉንም ምዕመናን ትብብር የሚጠይቅ ስለሆነ የዚህ ታላቅ በረከት ተካፋይ ለመሆን ሁላችንም እንበርታ፡፡

 

ቤተክርስያን ለመደገፍ እዚሀ ይጫኑ
ያግኙን

Facebook
Twitter
Youtube
የማመልከቻ ቅጽ

Address: 5  Grace Way, Ravenhall VIC 3023

©2016 - Debre Genet St Michael Church in Melbourne - Web Designed by - Gdey.com.au
  • Twitter
  • Facebook
Scroll to top