News

በኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋህዶ የሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ኅዳር 12 ቀን 2008 ዓ.ም. በተከበረው የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ የህንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ጳውሎስ ሁለተኛ (Catholicos of the East and Malankara Metropolitan) ፣ ዶክተር ዩሃኖን ማር ዲዮስቆሮስ (Metropolitan) ፣ የህንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቀሳውስትና ምዕመናን፣ በመላው አውስትራልያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ካህናትና ዲያቆናት፣ ከኢትዮጵያ ለአገልግሎት የመጡ ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ እና ዲያቆን መምህር ብርሃኑ አድማስ እንዲሁም ከመላው አውስትራልያ በተሰባሰቡ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ፡፡ ይህን ያደረገ የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን፡፡ አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ሁላችንንም በረድኤትና በበረከት ይጠብቀን፡፡